የደንበኞች ጥበቃ

JustforexGO ከተለያዩ ሀገራት ካሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞች የታመነና አስተማማኝ የፎሬክስ ደላላ (አገናኝ) ነው። በአሁኑ ጊዜ በእስያ ውስጥ በጣም ታዋቂ ከሆኑ ደላላዎች አንዱ ነን፣ እና በሌሎች ክልሎች ካሉ ተወዳዳሪዎች አናንስም።

አስተማማኝነት

የኩባንያው አስተማማኝነት የደንበኞችን ፍላጎት የማሟላት አቅም፣ እንዲሁም እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የስራ እና የአገልግሎት ጥራት ነው።

የሥራ መረጋጋት

የ JustforexGO የስጋት አያያዝ ቡድን ስኬታማ ስራ በማንኛውም የገበያ ሁኔታ ውስጥ የኩባንያውን የተረጋጋ ስራ ያረጋግጣል። የስዊዘርላንድ ማዕከላዊ ባንክ የ EUR/CHF የምንዛሬ ጣሪያን ለመሰረዝ ከወሰነ በኋላም ቢሆን፣ ይህም የዚህ የግብይት መሳሪያ ከፍተኛ መዋዠቅ ምክንያት የብዙ የፎሬክስ አገናኞችን የፋይናንስ ችግር አስከትሏል።

የታላላቅ ባንኮች ሊኩዊዲቲ

ለ JustforexGO ኩባንያ ሊኩዊዲቲ የሚቀርበው በ 18 ቱ ትላልቅ የዓለም ባንኮች ነው። በተጨማሪም የኩባንያው ደንበኞች እጅግ በጣም ጠቃሚ ለሆኑ ትዕዛዞች በእነዚህ ባንኮች ከሚቀርበው ተለዋዋጭ ዋጋ ምርጡን ዋጋ ብቻ ያገኛሉ።

ብቁ ሰራተኞች

የ JustforexGO ሰራተኞች በፋይናንስ ዘርፍ ከ 10 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ከፍተኛ ደረጃ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ሁልጊዜም ለመርዳት እና ለደንበኞች ብቁ የሆነ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

የተለዩ አካውንቶች

የ JustforexGO ደንበኞች ገንዘብ በተከፋፈሉ የባንክ አካውንቶች ውስጥ የሚቀመጥ ሲሆን፣ ይህም ማለት የ JustforexGO የራሱ ገንዘብ እና የደንበኞች ገንዘብ የተለያዩ ናቸው ማለት ነው።

ደህንነት

እያንዳንዱ ደንበኛ ከእኛ ኩባንያ ጋር ሲሰራ ገንዘቡ እና የግል መረጃው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንደሚቀመጥ እርግጠኛ መሆን አለበት።

የመረጃ ልውውጥ ጥበቃ

መረጃን በምስጢር ኮድ (encryption) በማድረግ በ SSL የደህንነት ግንኙነት በኩል መረጃን ማስተላለፍ፣ የትም ቦታ ቢሆኑ በድረ-ገጹ ላይ በሚሰሩበት ጊዜ የተጠቃሚ መረጃ በሶስተኛ ወገን እንዳይጠለፍ ይከላከላል።

ከዕዳ ቀሪ ሂሳብ ጥበቃ

የ JustforexGO ኩባንያ የደንበኞች ኪሳራ በንግድ አካውንታቸው ላይ ካለው የገንዘብ መጠን በላይ ሲሆን ማካካሻ ያደርጋል። ይህ ማለት በገበያው ላይ በሚፈጠር ድንገተኛ እንቅስቃሴ ምክንያት ቀሪ ሂሳብ ከዜሮ በታች ሲሆን፣ ደንበኞችን ካልተጠበቀ ኪሳራ ለመጠበቅ ሲባል ቀሪ ሂሳቡ ወደ ዜሮ ይመለሳል ማለት ነው።

ዓለም አቀፍ የደህንነት ደረጃ

የኩባንያው የውስጥ አሰራሮች በ (ፒሲአይ) PCI ዲኤስኤስ (DSS) የደህንነት ደረጃ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፣ ይህም የደንበኞችን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል የተራቀቀ አሰራርን ያካትታል።

ባለብዙ ደረጃ የሰርቨር ስርዓት

በርካታ ሰርቨሮችን ያካተተው መሠረተ ልማት፣ ሥርዓቱ ያለ ምንም መቆራረጥ እንዲሠራ ይረዳል። እንዲሁም የተራቀቀ የመረጃ መጠባበቂያ (backup) አሰራር ዘዴ፣ በማንኛውም ሁኔታ የደንበኞች መረጃ (የግል መረጃ፣ የንግድ ታሪክ ወዘተ) ከመጥፋት ለመከላከል ይረዳል።

የተቀመጡ መረጃዎች ጥበቃ

የተጠቃሚዎች መረጃ ጥበቃ የሚደረግለት በድረ-ገጹ እና በብሮውዘሩ መካከል በሚዘዋወርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ የተቀመጡ መረጃዎች በሙሉ በምስጢር ኮድ (encryption) እንዲቀመጡ እናደርጋለን፤ ይህም ያልተፈቀደላቸው አካላት የደንበኞቻችንን መረጃ እንዳያገኙ ለመከላከል ይረዳል።